Skip to content Skip to footer

POEMS Other

ዝሙረ ዳዊት 20   ወደር የሌለው በረከት

 

ክፉ ቀን ሲመጣ እግዚአብሄር ይቅረብህ

ከመአቱ ያውጣህ ጥበቃው አይራቅህ

እርዳታውን ይላክ፤ ሙሉ ፈውስን ይስጥህ

ከመቅደሱ ልኮ ጽጋውን ያውርስህ።

 በጸሎትህ ሁሉ ይደሰትብህ

በምሥጋናህ ሁሉ ደስ ይሰኝብህ፤

የልብህን ደስታ እና ምሥጋና፤

አይቶ ከፍ ያድርግህ፤ ልብህን ያሟላ።

 እስከ መጨረሻው በርሱ ተደስተን

አንድ ሕዝብ ያድርገን በጸጋው ያኑረን።

አቤቱታህ ሁሉ ከአፍህ ሳይወጣ

በረከቱን ሰጥቶህ ሁሉንም ያሟላ።

 እግዚአብሄር የቀባውን ሁሉ ያድናል፤

ከክፉ ሊጠብቅ ቀኝ እጁን አዞታል።

ጫፋቸው ሲነካ እጅጉን ይቆጣል፤

እንደመጫት ነብር በንዴት ያጓራል።

 ከእግዚአብሄር ይልቅ ላንዳንዱ መከታው

የጦር ሠራዊቱ፤ እንዲሁም መሣሪያው።

እንዲህ አይነቱ ባዶ ነው፤ ይወድቃል።

ከእግርህ ስር ሆኖ፤ ድልህን ያየዋል።

 የግዚአብሄር በረከት አይራቅ ከአንተ ቤት

ፈጥኖ ይድረስልህ ቀንም ሆነ ዕሌት።

1 Comment

  • Avatar
    Post Author
    sahlumikael
    Posted December 14, 2021 at 11:19 pm

    this is a wonderful poem

Comments are closed.